#Ethiopia | የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር አልጄሪያ ለዜጎቿ የዘረጋችው አስደናቂ የማህበራዊ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመላው አፍሪካ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈ ይገኛል።
ሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብቷን እና የኢኮኖሚ አቅሟን ቀጥታ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል በሚያስችሉ ዘመናዊ ውሳኔዎች ላይ በመመደብ በአፍሪካ አዲስ ምሳሌነቷን እያሳየች ነው።
ሀገሪቷ ስራ ለሌላቸው ወጣቶች በወር 96 ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች።
ይህ ድጋፍ ወጣቶች ስራ እስኪያገኙ ድረስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲሸፍኑ የሚያስችል ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ ነፃ የጤና መድህን አገልግሎትም ያካትታል ተብሏል።
በወር ከ 216 ዶላር በታች የሚያገኙ ዜጎች ምንም አይነት የገቢ ግብር እንዳይከፍሉ አድርጋለች።
በተጨማሪም አነስተኛ የደመወዝ ወለል ወደ 170 ዶላር ከፍ በማድረግ የዜጎችን የመግዛት አቅም እንዲሻሻል አድርጋለች።
ከዚህ በተጨማሪም ለህዝቧ በሙሉ ነፃ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አረጋግጣለች።
አልጄሪያ ግዙፍ የተፈጥሮ ጋዝ እና የሃይል አቅሟን በመጠቀም 100 በመቶ ለሚጠጉ ዜጎቿ ሙሉ በሙሉ ተራሽ እና ነፃ የሆነ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማድረስ ችላለች።
ይህም በገጠር እና በከተማ የሚኖሩ ዜጎቿ በእኩል መሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ነው የተባለው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Algeria #Africa #BreakingNews
#Economy #AfricanFolder
Source: GetuTemesgen









No comments yet.