7 ዓመቷ ፊዮና ሰለሞን በደህና ወደ ቤተሰቦቿ ተመለሰች!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በእገታ የተያዘችው 7 ዓመቷ ፊዮና ሰለሞን፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በሌሎች የጸጥታ ተቋማት በተደረገ የተቀናጀ ፍለጋ ከጎንደር ከተማ በደህና ተገኝታለች።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከአማራ ክልል ፖሊስ፣ ከጎንደር ከተማ ፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ያከናወነው ሥራ ፊዮናን ወደ ቤተሰቦቿ እንድትመለስ አስችሏል።

በተለይም የሕፃኗ ቤተሰቦች ፖሊስ ከልጃቸው መጥፋት ጀምሮ ቀንና ሌሊት ያደረገውን ፍለጋ በማድነቅ፣ “ልጃችንን በእጃችን በማስገባቱ ወደር የሌለው ደስታ ተሰምቶናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ፖሊስም ወንጀል ፈጻሚዎች ለጊዜው ከሰው ዓይንና ጆሮ ቢሰወሩም ከሕግ ማምለጥ እንደማይችሉ አስገንዝቧል።

ለፊዮና ደህንነት የተጨነቁ እና መረጃውን ሲከታተሉ ለነበሩ ሁሉ ይህ የምስራች ነው።

ፊዮና ወደ ቤተሰቦቿ በደህና በመመለሷ ደስ ብሎናል!

🙏 ለተሳተፉ የጸጥታ አካላትና ለመላው ማህበረሰብ ምስጋና!

#ፊዮና_ሰለሞን #የምስራች #አዲስአበባፖሊስ #ሕፃናት #Ethiopia #AddisAbaba #FionaSolomon #Justice #ጥንቃቄ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2