በኢትዮጵያ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድገት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው 8ኛው አግሮፉድ እና ፕላስትፕሪንትፓክ እንዲሁም 2ኛው የኢትዮጵያ የምግብና የኤክስፖርት የቡና ንግድ ትርዒት ጥምር ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ሙሉ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገለጠ ።
ይህ በዓነቱ ግዙፍ የሆነው የኢንዱስትሪ መድረክ በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት እያሳየች ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከብራዚል፣ ቻይና፣ ጣሊያን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ጨምሮ ከ18 በላይ ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ዓለም አቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎችን በአንድ ጣሪያ ስር የሚያገናኝ ልዩ ኹነት መሆኑ ተጠቁሟል ።
ዝግጅቱ በተለይም በምግብ፣ በግብርና፣ በቡና፣ በላስቲክና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ አዳዲስ ፈጠራዎችንና የንግድ ትስስሮችን ይዞ እንደሚቀርብ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል ።
ይህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም (June 25–27, 2026) በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ለሶስት ቀናት ተከፍቶ እንደሚቆይ ታውቋል ።
Source: FastMereja









No comments yet.