#Ethiopia | በዶሃ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 5,000 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አስደናቂ ብቃት በማሳየት ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉትን ደረጃዎች በመቆጣጠር ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።
በውድድሩ አትሌት Medina Eisa 14 ደቂቃ ከ53.91 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ርቀቱን በማጠናቀቅ የአንደኝነት ድልን ተቀዳጀች።
ከእርሷ በመቀጠል Liqenah Ambaw ሁለተኛ ደረጃን ስታገኝ፣ Marta Alemayo ሦስተኛ፣ Birnesh Dessie አራተኛ እና Hawi Abera አምስተኛ በመውጣት ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ ፍጹም የበላይነት ማሳየቷን አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል Melknat Wudu ሰባተኛ ደረጃን ስታገኝ፣ Aynadis Mebratu ዘጠነኛ እና Yenewa Nibret አስረኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቶች በዚህ ውድድር ያሳዩት ውጤት በረጅም ርቀት ሩጫ ያላቸውን ብቃትና በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ በድጋሚ ያረጋገጠ ሲሆን፣ መዲና ኢሳ ያስመዘገበችው ድል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሌላ አንጸባራቂ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
Source: GetuTemesgen








No comments yet.