በ2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ብር ይረጋጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ለፓርላማ ገለጹ
በዚህ በጀት ዓመት ብር በ15 በመቶ ቢቀንስም፣ በመጪው በጀት ዓመት የ9.8 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ይህ ዕድገት በግብርና (7.1%)፣ በኢንዱስትሪ (11.6%) እና በአገልግሎት (8.5%) ዘርፎች የሚመራ ነው።
ነገር ግን በሩቅ ምሥራቅ ግጭት ሳቢያ በጨመረው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት የሀገሪቱ የገቢ ዕቃዎች ወጪ 25.8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
ከዚህ ውስጥ 6 ቢሊዮን ዶላሩ ለነዳጅ የሚውል ነው።
መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋት አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጣ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ጨረታዎችንና የንግድ ባንኮችን ሚና በማጠናከር በሕጋዊና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ወደ 11 በመቶ ማውረድ መቻሉን ገልጿል።
እንዲሁም የውጭ ዕዳን መልሶ ለማዋቀር ድርድሮች እየተደረጉ ነው።
ካፒታል ጋዜጣ
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.