#Ethiopia | የምሽቱ ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በድህረ ግጥምያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ዘላለማዊ ተቀናቃኙ ሊዮኔል ሜሲ ለተነሳበት ጥያቄ የሰጠው ፈጣንና ቁልጭ ያለ ምላሽ በስፖርቱ ዓለም መነጋገሪያ ሆኗል።
አንድ የፈረደበት ጋዜጠኛ “ትናንት ሜሲ…” በማለት ገና ጥያቄውን መደርደር ሲጀምር ሮናልዶ የጋዜጠኛውን ንግግር ወዲያውኑ በማቋረጥ “ቀጣዩ ጥያቄ!” በማለት ፊቱን ከእርሱ አዙሯል።
ይህ አስገራሚ ክስተት በሁለቱ ድንቅ ኮከቦች መካከል ያለው ለዓመታት የዘለቀ የፉክክር ስሜት አሁንም እንዳልበረደ የሚያሳይ ሲሆን ሮናልዶ ከእሱ ውጭ ስለ ሌላ ተጫዋች የሚነሱ ወሬዎችን ለማድመጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን በግልጽ ያሳየበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.