“ቀጣይ ጥያቄ!” — ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ስለ ሜሲ ሊሰማ አልፈቀደም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የምሽቱ ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በድህረ ግጥምያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ዘላለማዊ ተቀናቃኙ ሊዮኔል ሜሲ ለተነሳበት ጥያቄ የሰጠው ፈጣንና ቁልጭ ያለ ምላሽ በስፖርቱ ዓለም መነጋገሪያ ሆኗል።

አንድ የፈረደበት ጋዜጠኛ “ትናንት ሜሲ…” በማለት ገና ጥያቄውን መደርደር ሲጀምር ሮናልዶ የጋዜጠኛውን ንግግር ወዲያውኑ በማቋረጥ “ቀጣዩ ጥያቄ!” በማለት ፊቱን ከእርሱ አዙሯል።

ይህ አስገራሚ ክስተት በሁለቱ ድንቅ ኮከቦች መካከል ያለው ለዓመታት የዘለቀ የፉክክር ስሜት አሁንም እንዳልበረደ የሚያሳይ ሲሆን ሮናልዶ ከእሱ ውጭ ስለ ሌላ ተጫዋች የሚነሱ ወሬዎችን ለማድመጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን በግልጽ ያሳየበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1