በሆርሙዝ ሰርጥ ለወራት ተይዛ የነበረችው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መርከብ “MV ጊቤ” በሰላም ወደ አገር ቤት እየተመለሰች መሆኑ ተገለጸ።
በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ምክንያት ጉዞዋ ተስተጓጉሎ የቆየው መርከቧ፣ በአሁኑ ወቅት ከጭነቷ ጋር ወደ ጅቡቲ ወደብ በመጓዝ ላይ መሆኗ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ምልክት የሆነችው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ከሚያውለበልቡ መርከቦች አንዷ የሆነችው MV ጊቤ፣ በአሁኑ ወቅት በኦማን ገልፍ አካባቢ የምትገኝ ሲሆን፣ የፊታችን ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ወደ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል።
Via capital
Source: Yeneta Tube









No comments yet.