ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ያመረተችውን ጥይት ወደ ውጭ መላክ ጀመረች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ማምረት የጀመረችውን ቀላልና ከባድ የጦር መሣሪያዎች ጥይት ለጎረቤት ሀገራት መላክ መጀመሯንና በዚህም አዲስ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሏን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። ሀገሪቱ የጸጥታ መዋቅሯን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀትና ወታደራዊ ቁሶችን በራስ አቅም ለማምረት የጀመረችው ታሪካዊ እርምጃ በወታደራዊ ዘርፍ የነበራትን የዓመታት የውጭ ጥገኝነት በመቀነስ የራሷን ፍላጎት በራሷ የምትፈታበትን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ ስኬት በድንገተኛ የጸጥታ ተግዳሮቶች ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የመሣሪያና የጥይት አቅርቦት እጥረት አስተማማኝ ዋስትና ከመስጠቱም በላይ ቀደም ሲል ለውጭ ግዥ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማዳን እንደቻለ ሠራዊቱ ገልጿል።

​ከጥይት ምርት በተጨማሪ መንግሥት የድሮን ቴክኖሎጂን በአገር ውስጥ የማልማትና የመገጣጠም ሥራን በስፋት እየተገበረ ይገኛል። እነዚህ የተቋቋሙት የድሮን ማዕከላት መከላከያ ሠራዊቱ የሀገሪቱን አየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲቆጣጠር ትልቅ አቅም የፈጠሩ ሲሆን፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የጸጥታ ስጋቶችንም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችለዋል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ያሳዩት ይህ አዲስ እመርታ፣ ሀገሪቱ በወታደራዊ መስክ ራሷን ከመቻል አልፋ ወደ ውጭ ላኪነት የተሸጋገረችበትን ትልቅ ስኬት የሚያሳይ ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: