#FastMereja I በሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ ተዋናዮች መካከል ያለውን ትስስር፣ መነቃቃት እና ጤናማ ውድድር ለማጠናከር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው «ኢትዮ ሪል እስቴት ካፕ» ውድድር ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ፍፃሜውን አግኝቷል።
በአርኪ ኢቨንትስ ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየውና በርካታ የዘርፉ ተወካዮችና ተቋማት የተሳተፉበት ይህ ውድድር፤ የፍፃሜ ጨዋታውን ዛሬ በ24 ሜዳ ላይ በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።
ብርቱ ፉክክር በተስተዋለበት የፍፃሜ ጨዋታ ጃንቦሮ ሪል እስቴት ተጋጣሚውን ቴምር ሪል ስቴትን 2 ለ 1 በማሸነፍ የዘንድሮው የ«ኢትዮ ሪል እስቴት ካፕ» ባለቤት መሆን ችሏል። በውጤቱም የክብሩ ባለቤት የሆነበትን ዋንጫ፣ የወርቅ ሜዳሊያ እና የ300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።
የዘርፉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተቋማት ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞችና በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት በዚህ የፍፃሜ ፕሮግራም ላይ ውድድሩ በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል። ለባለዋንጫው ጃንቦሮ ሪል እስቴት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እናስተላልፋለን!



Source: FastMereja









No comments yet.