“ተመራቂዎች ስራ ፈላጊ ብቻ ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን ለሀገራችሁ ሰላምና ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባችኋል” ታፈረ ከበደ

- Advertisement -
Sidebar AD

“ተመራቂዎች ስራ ፈላጊ ብቻ ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን ለሀገራችሁ ሰላምና ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባችኋል” ታፈረ ከበደ

ሜድስኬፕ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን አስመርቋል።

በምርቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዊ ብሄ/አስ ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ታፈረ ከበደ፥ ከብዙ ልፋትና ውጣውረድ በኋላ ለምርቃ በመብቃታቹህ እንኳን ደስአላቹህ ብለዋል።

መማር ማለት እውቀትን ወደ ተግባር የምንቀይርበት ሰፊ አውድ ነው ያሉት ሀላፊው መልካም ነገርን በመለማመድ የተሻለ አስተሳሰብ እና ስነ-ምግባር መገንባት እንደሆነም ተናግረዋል ።

በመሆኑም እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች የተሻለ አመለካከትን በመገንባት ለሀገራችን እድገትና ሰላም የበኩላቸሁን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።

ዘመኑ የዲጂታል በመሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ስራ ፈላጊ ብቻ ሳትሆኑ ስራ በመፍጠር ለሀገራችሁ ሰላምና እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባችኋል ነው ያሉት።

ወደስራው ዓለም ስትገቡ ሙያችሁን በማክበር ህዝቡን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆን አለባችሁ ብለዋል።

በመጨረሻም በመርሀ ግብር ተምረው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል።

ተማሪ ሐና ሹመቴ በ2018 የሜድስኬፕ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ተመራቂዎች የዋንጫ ተሸላሚ ሁናለች።

ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን 5 ምሩቃን በኮሌጁ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1