ኮንጎም ልክ እንደ ኢትዮጵያ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ዕድገት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን እርምጃ በመውሰድ የመጀመሪያዋን የአክሲዮን ገበያ በቀጣዩ ዓመት በይፋ ልትከፍት መሆኑን አስታውቃለች።

ይህ አዲሱ የአክሲዮን ገበያ ግብይቱን በሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ በሆነው በኮንጐ ፍራንክ እና በአሜሪካ ዶላር የሚያካሂድ ሲሆን ዋነኛ ዓላማውም በተለይም በማዕድን ዘርፍ እና በሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ መስኮች ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንትን መሳብ ነው።

​በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ኮፐር፣ ኮባልት እና ሊቲየም ለመሳሰሉ ወሳኝ ማዕድናት ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣቱ ይህ የፋይናንስ ገበያ መከፈቱ ለኮንጎ የንግድ ተቋማት ሰፋፊ የፋይናንስ ማግኛ አማራጮችንና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ተስፍ ተጥሎበታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ቀደም ብላ የካፒታል ገበያውን መበላቀሏ ይታወሳል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1