የታዋቂው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ተወዳጅ የራዲዮ

- Advertisement -
Sidebar AD

ዝግጅት “መቆያ” በመጽሐፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ

#Ethiopia | ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት እና እሁድ ምሽት በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ጣቢያ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተላልፍ የቆየውና በአድማጮች ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው “እነሆ መቆያ” ፕሮግራም በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ለገበያ መቅረቡ ተገለጠ።

በአንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ የሚዘጋጀውና የበርካታ ግለሰቦች፣ አገራት እንዲሁም የተለያዩ ክስተቶች እውነተኛ ታሪኮችን በልዩ የአቀራረብ ስልቱ ሲያስደምጥ የነበረው ይህ ዝግጅት፣ አሁን ላይ ከአድማጮች አልፎ ለአንባቢያን እንዲደርስ ተደርጓል።

ይህ ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችንና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችን አቅፎ የያዘው ልዩ የራዲዮ ትውስታ፣ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሑፍ ዓለም በመሸጋገር ለአንባቢያን የተለየ የስሜት ጉዞን እንደሚያበረክት ታውቋል።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረው የጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” መጽሐፍ በአሁኑ ወቅት በጃፋር መጻሕፍት መደብር ውስጥ ለሽያጭ መቅረቡ ተረጋግጧል።

#እነሆመቆያ #እሸቴአሰፋ #ሸገርኤፍኤም #አዲስመጽሐፍ #ጃፋርመጻሕፍት #ኢትዮጵያ





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: