የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ገቢ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ3 ቢሊዮን ዶላር ጣሪያን በመንካት አስደናቂ ስኬት አስመዝግቧል።

የቡና ወጪ ንግድ ገቢው የተረጋጋና ተከታታይነት ያለው ዕድገት እያሳየ የመጣ ሲሆን በ2023 ከነበረው 1.4 ቢሊዮን ዶላር በመነሳት በዘንድሮው በጀት ዓመት ይህንን ታሪካዊ የገቢ መጠን ሊያሳካ ችሏል።

​ለዚህ ታላቅ ስኬት መመዝገብ በቡና የእሴት ሰንሰለት ውስጥ በሚሳተፉ አካላት ማለትም በአርሶ አደሮች፣ በላኪዎች፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ በባለሀብቶች እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተደረገው የተቀናጀ ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ የገበያ መድረክ ጥራት ላለው ቡና የሚቀርበውን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላት ሲባል፣ መንግሥት በሀገር ውስጥ የቡና ማቀነባበርና እሴት ጭማሪ፣ በጥራት ቁጥጥር፣ በምርት መከታተያ ሥርዓት እና በማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራቱ ለዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2