በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተባለ፡፡
በሳምንት ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 604 ወንዶችና 1መቶ92 ሴቶች አመት እንዲሁም 38 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 53 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡
ወደፊትም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት ሚኒስቴሩ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።
በአጠቃላይ 1ሺህ 8መቶ 34 ዜጎች ወደ አገር ዉስጥ ተመልሰዋል መባሉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.