አንቀጽ 39 እስከ መገንጠል የሚለው እስከ መዋሃድ ተብሎ እንዲስተካከል ሐሳብ ቀረበ
የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ቀርቶ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ኮሚሽን የሚል ተቋም እንዲቋቋም ተጠይቋል
በአገራዊ ምክክር ጉባዔ በአሥርና በ50 ተመካካሪ ቡድን ሲወያዩ የቆዩ ተመካካሪዎች ያጠናከሩትን የአጃንዳ ሐሳብ፣ 250 አባላት ላሉት የምክክር ቡድን ማቅረብ ሲጀምሩ፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት “እስከ መገንጠል” በሚለው አንቀጽ 39 ስር የተቀመጠው ሐረግ “እስከ መዋሃድ” ተብሎ እንዲስተካከል የሚል ሐሳብ ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ቀረበ።
ሀሳቡ የቀረበው፣ አሥርና 50 አባላት ባላቸው ንዑሳን ቡድኖች ስር ሲወያዩ የቆዩ ተመካካሪዎች፣ 250 አባላት ላሉት ሥልታዊ ቡድን ያጠናቀሩትን የአጀንዳ ሐሳብ ሲያቀርቡ ነው።
በዚህም ሐሳብ ከቀረበባቸው አጀንዳዎች መካከል፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓትን የተመለከተው አንዱ ሲሆን፣ በሥሩም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት (የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት አንቀጽ 39) ንዑስ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል።
ይህ ንዑስ አጀንዳ(አንቀጽ 39)፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ሙሉ ለሙሉ ሳይሻር “እስከ መገንጠል” የሚለው ሐረግ ብቻ ከድንጋጌው እንዲወጣና ባለበት እንዲቀጥል የሚጠይቁ ሐሳቦች ከአሥርና ከ50ዎቹ ንዑስ ብድኖች በአብዛኛው ቀርበዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.