በኢትዮጵያ የአሳንሰር ችግርን የሚቀርፍ ግዙፍ የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈረመ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja | ሀገር በቀሉ ሞናጎ ኢሊቬተር እና የቱርኩ ኬ አር ሲ ኢሊቬተር በኢትዮጵያ የአሳንሰር (ሊፍት) ማምረቻ ፋብሪካ በጋራ ለመገንባት የሚያስችላቸውን የኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ዛሬ ፈረሙ። ላለፉት አምስት ዓመታት በትብብር ሲሰሩ የቆዩት ሁለቱ ኩባንያዎች፣ በተለይም ከሽያጭ በኋላ የሚታየውን የጥገና እና የስፔር ፓርት አቅርቦት እጥረት በመቅረፍ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ተስማምተዋል።

የሞናጎ ኢሊቬተር ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ኢሳያስ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት፤ አዲሱ አጋርነት በሀገሪቱ በግዢና በጨረታ የሚገጠሙ ሊፍቶች በቂ የጥገና አገልግሎት ባለማግኘታቸው ምክንያት የሚያጋጥማቸውን የስራ ማቆም ችግር በዘላቂነት ይፈታል። አቶ ተስፋሁን አክለውም፣ የመንግስትን የመሬት አቅርቦት ድጋፍ በመጠቀም የሚገነባው ፋብሪካ የቱርኩን የላቀ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን በማመቻቸት የቴክኖሎጂ ሽግግርን ዕውን እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ፋብሪካው ምርቱን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ማምረት ሲጀምር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባሻገር፣ በህንፃዎች ላይ የሚገጥሙ የአሳንሰር ብልሽት እና የስራ ማቆም ችግሮችን በማስወገድ በኢንዱስትሪው ውስጥ አዲስ ደረጃ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1