በሴኔጋል የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ፈጽመዋል በተባሉ 71 ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ሴኔጋል በግብረ-ሰዶማውያን ላይ የምታደርገውን ጥብቅ እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ በማጠናከር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ፈጽመዋል ባቻቸው 71 ወንዶች ላይ ይፋዊ ክስ መሥረታለች።

የአገሪቱ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው ከነበሩት መካከል የ28 ሰዎች ክስ የተቋረጠ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከየካቲት ወር ጀምሮ በእስር ላይ የነበረ አንድ የፈረንሳይ መሐንዲስ ይገኝበታል።

ሆኖም አቃቤ ሕግ የዚሁ ፈረንሳዊ መሐንዲስ ክስ መቋረጡን በመቃወም ይግባኝ ብሏል።

​ሴኔጋል ባለፈው መጋቢት ወር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ የሚጣለውን የእስራት ቅጣት ከ5 እስከ 10 ዓመታት የሚያሳድግ አዲስ ሕግ ማጽደቋ የሚታወስ ሲሆን ይህንን ተከተሎም ባለፉት ወራት ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: