“በውጤቱ ብደሰትም ገና የሚቀሩን ነገሮች አሉ” — ሚኬል አርቴታ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ባስመዘገበው ውጤት ደስተኛ ቢሆኑም፣ ስብስባቸው ፍጹም ለመሆን ግን ገና መስተካከል ያለባቸው “የቤት ስራዎች” እንዳሉበት በግልጽ ተናግረዋል።

​አሰልጣኙ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሰጡት አስተያየት የቡድናቸውን ጥንካሬ እና ድክመት እንዲህ አብራርተዋል፦

ተጫዋቾቻቸው በሜዳ ላይ ያሳዩት ስነ-ምግባር እና ሳይፈሩ ለመጫወት ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ከጨዋታው የሚፈለገውን ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት መቻላቸው ትልቅ ስኬት መሆኑን አምነዋል።

​አርቴታ ለድሉ እውቅና ቢሰጡም፣ ቀጣይ ስራዎቻቸው ላይ ግን ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡

​ ቡድኑ የሚያገኛቸውን ወርቃማ የጎል እድሎች በአግባቡ መጠቀም ላይ ክፍተት እንዳለበት ጠቁመዋል።

​ኳስ በጠፋባቸው ወቅት በፍጥነት ተጭኖ በመንጠቅ ረገድ ከዚህ የተሻለ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

​ተቃራኒ ቡድን ወደ ማጥቃት በሚሸጋገርበት ወቅት የሚሰነዝራቸውን ጥቃቶች ቀድሞ በማቋረጥ ረገድ መሻሻል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: