የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው ህክምና ማድረጋቸውን አስታወቁ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው ህክምና ማድረጋቸውን አስታወቁ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው እንደነበርና ለህመሙም አስፈላጊውን ህክምና ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።
“ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የፕሮስቴት ካንሰር እንዳለባቸው በምርመራ መረጋገጡንና ወዲያውኑ ወደ ህክምና መግባታቸውን ተናግረዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ህመሙ በጊዜ በመገኘቱና አስፈላጊው የህክምና ክትትል በመደረጉ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ኔታንያሁ ይህን መረጃ ያጋሩት ግልፅነትን ለመፍጠርና ስለ ጤንነታቸው የሚወጡ መረጃዎችን ለማጥራት እንደሆነ ተመልክቷል።
የ75 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከህክምናው ጎን ለጎን መደበኛ የመንግስት ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም መረጃዎች ያመለክታሉ።
ይህ መረጃ እስራኤል በከፍተኛ ቀውስና ጦርነት ውስጥ ባለችበት ወቅት መውጣቱ በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ትኩረትን ስቧል ሲል አል-አረቢያ ዘግቧል ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: