#Ethiopia | በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃን ያለው የለንደን ማራቶን ነገ ለ46ኛ ጊዜ ደረጋል፡፡ ከሰባቱ ሜጀር ማራቶኖች አንዱ በሆነውቤለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ የክብረ ወሰን ባለቤቷና የባለፈው ዓመት አሸናፊዋ ትዕግስት አሰፋ፣ ክብሯን ለማስጠበቅና ትሮጣለች፡፡
አትሌቷ የበርሊን ማራቶንን ሁለት ጊዜ ስታሸንፍ በፓሪስ ኦሎምፒክ ደግሞ የብር ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡ ትዕግስት በባለፉት 6 የማራቶን ውድድሮቿ ከሁለተኛነት ያነሰ ውጤትም የላትም፡፡
ከ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በተጨማሪ እንደ አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና አትሌት ባለምላይ ሹመት ያሉ አትሌቶች ከኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ ጋር ብርቱ ፍልሚያ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በወንዶች በኩል ደግሞ የፓሪስ ኦሎምፒክ አሸናፊው ታምራት ቶላ፣ ለአምስተኛ ጊዜ በለንደን አደባባይ ብቃቱን ለማሳየት ይሮጣል። የዓለም ሻምፒዮኑ ታምራት ከዚህ ቀደም በነበሩት ተሳትፎዎቹ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ለዘንድሮው የአሸናፊ ግምት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።
በውድድሩ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሮጥ ሲሆን ፣ ደሬሳ ገለታም ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዱ ነው።
ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ እንዲሁም የዩጋንዳውያኑ ጃኮብ ኪፕሊሞ እና ጆሽዋ ቼፕቴጋይ መገኘት ውድድሩን እጅግ አጓጊና ፈታኝ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#EthiopiaBroadcastingCorporation
Source: GetuTemesgen









No comments yet.