ሞዴል ናርዶስ አበበ በጋና የሚገኘው “ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን” (The Street of Gold Foundation) ከ”ማይስ ጋና” (MICE Ghana) እና ከ”ስቱዋርት ኤም.ሲ.ኢ ሊሚትድ ኢንተርናሽናል” (Stuart MCE Limited International) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መርሃግብር የ 2026 ተፅዕኖ ፈጣሪ በመባል በሁለት ዘርፎች አሸንፋለች፡፡
ሞዴሊስቷ በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን ወክላ በአለም አቀፍ ደረጃ በሞዴሊንግ እና በተለያዩ ልዩ ስጦታዋች በምታገኛቸው ድጋፎች ዘር ፣ቀለም እና ሃይማኖት ሳትለይ ድጋፍ የሚሹ ኢትጵያዊያንን እየደገፈች ትገኛለች።
“በዚህም የተነሳ ላበረከተቻቸው መልካም ነገሮች በዝግጅቱ ላይ አሸናፊ ሆናለች፡፡ እንደዚህ አይነት ሽልማቶች የሚያስገኙት ደግሞ በሞዴሊንግ፣በጋዜጠኝነት፣በአርት እንዲሁ በሌሎች ዘርፎች ልዩ ስጦታ ያላቸው ከሆነ ነው።
በዚህም የተነሳ በእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ በመካተት የሽልማቱ እድለኛ ሆናለች። ልዩ ስጦታ ላላቸው ሴቶች የሽልማት መረሃ ግብሩን ያዘጋቸው ዘ ስትሪት ኦፍ ፋውንዴሽን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም 11ኛ አውደ ርዕይ አካሂዷል ።
ሞዴል ናርዶስ ምንም እንኳን የሁለት የጎልድ ዋንጫ ተሸላሚ ብትሆንም፣እሷን ጨምሮ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ተሸላሚ ሆነዋል። ሞዴል ናርዶስ ባለትዳር እና የአራት ልጆችና እናት ስትሆን በቲክታክ ገጿም ከ700 ሺህ በላይ ተከታዮችን ያፈራች ናት ።
ይህንን ፔጅ በመጠቀም የተለያዩ ድጋፎችን ከተከታዮቿ በመሰብሰብ አጋዥ ለሌላቸው ህፃናት፣ሴቶች፣አቅመ ደካሞች የበኩሏን አስተዊፅኦ እያደረገች ትገኛለች።
በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በመልካም ስራ ኢትዮጵያን ወክሎ የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኜት ከራስ ደስታ በላይ ለሃገር ያለው ኩራት ከፍተኛ መሆኑን ሞዴል ናርዶስ ተናግራለች።
በቅርቡም ኢትዮዮጵያዊያና ጀርመናዊ በጋራ ሆነው ሆፕ ፎር ኦል (Hop For All) የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት በእናቶችና በህፃናት ዘርፍ ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ተደርጎ በተዋቀረ ድርጅት አጋር ሆና እንደምትመጣም እና አጋዥ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊን ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቁማለች።
ሞዴል ናርዶስ ከ16 ዓመቷ ጀምራ ኢትዬጵያን በመወከል በሞዴሊስት ዘርፍ በመወዳደር ጥረት ስታዳረግ መቆየቷንም እንዲሁም እንደ ሚስ -አፍሪካ ባሉ ውድድሮች በአምስተኛ ደረጃነትን በመያዝ (Top Five ) በመውጣት አጠናቃለች።
በተጨማሪ በተለያዩ ድርጅቶች ላይ በፍቃደኝነት በመሳተፍ በካንሰር፣ በኦቲዝም የተጠቁ ሰዎች እንደምታግዝ ተናግራለች።
በሌላ በኩል ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዲሽን ዋና መስራች ማጀስትይ ሮያል ፓንፎርድ እንደገፁት ከሆነ፣ ይህን አውደ ርዕይ ለማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያትም በተለዬ መልኩ ሴቶች በግብርናው፣ በበጎ ስነምግባር፣ በሞደሌንግ፣ በኢንዱስተሪያ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ያላቸው ተነሳሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ድግፉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም የተነሳ የዘንድሮው አውደ ርዕይ ላይ 6 ኢትዮጵያዊን ሴቶች ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ በድምሩ ለ20 ሴቶች የተለያዩ ሽልማቶችን ድርጅቱ ለማበረታት በማለም ድጋፍ ማድረጉን ግልጸዋል፡፡
በዚህ አውደ ረዕይ ላይ ከ120 በላይ የሚሆኑ በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅት ሃላፊዎችና ተስጦ ያላቸው አፍሪካዊን ተሳትፈዋል።



Source: FastMereja









No comments yet.