የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ቁንጮ መሆኑን የሚያስመሰክር የ2026 የአፔክስ የክብር ሽልማት ተቀዳጀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቱ ያለውን ቀዳሚነት የሚያረጋግጥ የአፔክስ የመንገደኞች ምርጫ የ2026 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን በድጋሚ ወስዷል፡፡

ይህ ሽልማት ተቋሙ ለተሳፋሪዎቹ የሚሰጠውን ምቹ፣ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ዓለም አቀፍ እውቅና የሰጠ ሲሆን በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ይበልጥ እንደሚያጎላው ተመልክቷል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሽልማቱን በተረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ስኬት የተመዘገበው በመላው የአየር መንገዱ ሰራተኞችና አመራሮች ከፍተኛ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሽልማቱ በቀጥታ በመንገደኞች ድምፅና ምርጫ የተሰጠ መሆኑ ልዩ ትርጉም እንደሚሰጠው የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው በቀጣይም የደንበኞችን አመኔታ ለማርካትና የአገልግሎት ጥራትን ይበልጥ ለማዘመን ከፍተኛ መነሳሳትን እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

#EthiopianAirlines #Aviation #AfricaBestAirline #ApexAwards #FlyEthiopian #EthiopianNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1