የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጥ ማሳሰቢያ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያከናወነ ባለው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ምክንያት፣ እሁድ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 9፡00 እስከ 10፡30 ድረስ ለአንድ ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃ የአገልግሎት መቋረጥ እንደሚኖር አስታውቋል። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የኮር ባንኪንግ፣ የሞባይል እና የኢንተርኔት ባንኪንግ፣ የኤ.ቲ.ኤም፣ የፖስ ማሽኖች እንዲሁም ከሶስተኛ ወገኖች ጋር የተገናኙ የበይነ መረብ አገልግሎቶች በሙሉ ለጊዜው የማይሰሩ መሆኑን ባንኩ ገልጿል።
ይሁን እንጂ በዚህ የጥገና ወቅት የሲቢኢ ብር አገልግሎት ያለምንም መቋረጥ በመደበኛ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ደንበኞች ይህንን የአጭር ጊዜ የአገልግሎት መቋረጥ አውቀው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ባንኩ ጥሪውን አስተላልፏል።
@seledadotio

No comments yet.