የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው የሚዲያ ዘርፉ ውጤቶች ለሀገራዊ ትርክት ግንባታ ስላላቸው ፋይዳ ማብራሪያ ሰጡ
#Ethiopia | በሚዲያ ዘርፍ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው በሚዲያው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ለተቋማቸው ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በዝርዝር አቅርበዋል።
ተቋሙ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አማካኝነት ብቁ እና ተወዳዳሪ ከመሆኑም ባለፈ ሙያዊ ነጻነቱ እንዲከበር ማድረግ ተችሏል።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የይዘት ጥራትን በማሻሻል፣ አደረጃጀቱን ዘመናዊ በማድረግ እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን በስፋት በመጠቀም ተደራሽነቱንና ተወዳዳሪነቱን አሳድጓል።
ተቋሙ ከለውጡ ሂደት ያገኘውን ልምድና ሰፊ የብሮድካስት ክህሎት ለሌሎች አካላት በማካፈል ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በተጨማሪም የሀሳብ ብዝሃነትን በማስተናገድ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታት እና አለም አቀፋዊ እይታን በማስፋት ተመራጭና ወቅታዊ የመረጃ ምንጭ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
#የሚዲያሪፎርም #ፋናሚዲያ #መረጃ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.