የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር ቴህራን የኒውክሌር መሣሪያ ሊኖራት እንደማይገባ መስማማታቸውን ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቱ የሁለት ቀናት ጎብኝታቸውን አጠናቅቀው ከመመለሳቸው በፊት በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ከፕሬዚዳንት ዢ ጋር “ሌሎች ሊፈቱት የማይችሉትን በርካታ ችግሮችን ፈትተናል” ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ጋር በኢራን ጦርነት፣ በታይዋን፣ በንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ዢ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ስላደረጓቸው ውይይቶች በዝርዝር የተናገሩት ነገር የለም።
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን የዘጋችው የአሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት በመሆን ጦርነት ከከፈቱባት በኋላ ነው።
የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የዓለም የኢነርጂ አቅርቦት ላይ መስተጓጎልን በመፍጠር የዋጋ ንረት አስከትሏል።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ለከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ “ይህ መፈጠር ያልነበረበት ግጭት፣ የሚቀጥልበት ምክንያት የለም” ብሏል።
ትራምፕ በፎክስ ኒውስ “ሃኒቲ” ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ቴህራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት መሟጠጡን ሲገልጹ “ከዚህ በላይ ትዕግሥት ሊኖረኝ አይችልም። ከስምምነት መድረስ አለባቸው” ብለዋል።










No comments yet.