ቡካዮ ሳካ ለተቺዎቹ ምላሽ ሰጠ
#Ethiopia | “ለ22 ዓመታት ሲስቁብንና ሲቀልዱብን ነበር… አሁን ግን መሳቅ አቁመዋል!” — ቡካዮ ሳካ
ትናንት ማንቸስተር ሲቲ በቦርንማውዝ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነቱን ማረጋገጡ ይታወሳል።
ከዚህ ታሪካዊ ድል በኋላ የተናገረው የ24 ዓመቱ የክለቡ ምክትል ካፒቴን ቡካዮ ሳካ፣ ለአመታት በክለቡና በደጋፊው ላይ ይደርስ የነበረውን ስድብና ማሾፍ አስታውሶ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥቷል።
የቡካዮ ሳካ ድንቅ የአርሰናል ታሪክ (All-Time Stats)
* 🏟️ 311 የተጫወታቸው ጨዋታዎች
* ⚽️ 81 ጎሎች
* 🅰️ 71አሲስቶች
* 🎯 152 ጎል እና አሲስት (G/A) በቀጥታ የተሳተፈባቸው!
ከ”ስታር ቦይ” እስከ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን
ሳካ ገና በ8 ዓመቱ ወደ አርሰናል አካዳሚ ለሙከራ ሲመጣ፣ አባቱ በራስ መተማመን ኖሮት እንዲጫወት “King Kayo” የሚል ጽሑፍ ያለበት ማሊያ አልብሶት ነበር። በ2013 መጀመሪያ አርሰናልን ሲቀላቀል “እዚህ ክለብ ውስጥ ኮከብ (Star Boy) መሆን እፈልጋለሁ” ብሎ የነበረው ሳካ፣ ከ16 ዓመታት ረጅም ጥረት በኋላ ዛሬ የልጅነት ክለቡን ለታላቁ የሊግ ዋንጫ ክብር አብቅቷል!
የእውነት የሳካ ንግግር የእያንዳንዱን መድፈኛ ስሜት የነካ ነው። ያኔ ‘ስታር ቦይ’ እያልን ስንቀብጠው የነበረው ልጅ ዛሬ የአርሰናል ምክትል ካፒቴን ሆኖ ዋንጫውን አንስቷል።
22 ዓመታት ሙሉ ‘አርሰናል ዋንጫ አያነሳም’ እያሉ ሲቀልዱብን ለነበሩት ተቺዎች ሁሉ ሳካ በሜዳ ላይም በአደባባይም የማይረሳ መልስ ሰጥቷቸዋል። አሁን ሳቁ ወደ እኛ ዞሯል።
ምንጊዜም ድል ለመድፈኞቹ!”
#getu #BukayoSaka #ArsenalChampions #StarBoy #KingKayo #PremierLeague2026 #COYG #SakaStats #SakaSpeech #አርሰናል #ቡካዮሳካ #ሻምፒዮን #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen









No comments yet.