የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለአርሰናል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ የዓመታት ጥረትና ትግል ፍሬ አፍርቶ የኢንግሊሽ ፕሪሚየር ሊግ የክብር ማዕረግን በመቀዳጀቱ፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለክለቡና ለደጋፊዎቹ ልባዊ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አጋርተዋል።

​ፕሬዝዳንት ሩቶ የአርሰናልን የዓመታት ጉዞ “ከውድቀትና ከከባድ ፈተናዎች ተነስተው፣ ተስፋ ባለመቁረጥና በማይናወጥ ጥንካሬ ወደ እግር ኳስ ማማው ማደግ የቻሉበት ታላቅ ጀብዱ” ሲሉ አሞካሽተውታል።

ክለቡ በየሳምንቱ ከተፎካካሪዎች ጋር ያደረገው ፍልሚያ የተስፋን፣ የፅናትን እና የጠንካራ ስራን ኃይል በተግባር ያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል።

​ፕሬዝዳንቱ አክለውም፥ “በደማቁ ምሽት ያ ታላቅ ጥረት ፍሬ አፍርቷል፤ ቡድኑም የድሉ ባለቤት ሆኗል። ለዓመታት የነበራቸው እምነትና ቁርጠኝነት በተግባር ተመስክሯል። ይህ ድል በጠንካራ ስራ፣ በዲሲፕሊን እና በቡድን መንፈስ ስኬትን ማምጣት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው” በማለት የአርሰናልን ስኬት አጣጥመዋል።

​በመጨረሻም ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “እንኳን ደስ አላችሁ መድፈኞቹ)!” በማለት መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#Arsenal #COYG #PremierLeagueChampions #WilliamRuto #Gunners #FootballNews #EPL #ArsenalFC


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: