የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ
#Ethiopia | ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኀንና የሲቪል ማህበራት ሚና ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ መልካ አዳማ ሆቴል እየተካሄደ ነው።
“ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኀን ሚና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ይህንን መድረክ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ አዘጋጅተውታል።
በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበራት መሪዎች እና የብዙሃን መገናኛ ተወካዮች ታድመዋል።
ከየመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ፣
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፣ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ሃላፊዎችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫን ማካሄድ የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ለማስገንዘብና በሂደቱ ውስጥ የመገናኛ ብዙኀን እና የሲቪል ማህበራት ያላቸውን ወሳኝ ሚና ለመቃኘት እንደሆነ ተገልጿል።
#አዳማ #ምርጫ2018 #የመገናኛብዙሃን #ኢትዮጵያ #Ethiopia #MediaRole

Source: GetuTemesgen









No comments yet.