የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና የሲንቄ ባንክ ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እያከናወናቸው ያሉትን የቤት ልማትና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም የፋይናንስ አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከሲንቄ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ላይ እያበረከተ ያለውን በጎ አስተዋጽኦ ለማስፋት እና ዘመናዊ የቤት ልማት ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት እያጠናከረ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ዛሬ የተደረሰው ስምምነት ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውናቸው ሰፊ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች የሚውል የፋይናንስ አቅርቦት ማመቻቸትን የሚያካትት ሲሆን፥ ሁለቱ ተቋማት በሌሎች ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል።

በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል፣ የሲንቄ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ንዋይ መገርሣ እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በወቅቱም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እንደገለጹት፤ ይህ ስምምነት ኮርፖሬሽኑ የጀመራቸውን ግዙፍ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች በላቀ የፋይናንስ አቅም ለመደገፍ እና የተቋሙን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

#የፌደራልቤቶችኮርፖሬሽን #ሲንቄባንክ #የቤትልማት #ኢንቨስትመንት #ፋይናንስ #ባንክ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1