በነገሌ ቦረና የተገነባው የገዳ አውሮፕላን ማረፊያ  ተመረቀይህ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በነገሌ ቦረና የተገነባው የገዳ አውሮፕላን ማረፊያ  ተመረቀ
ይህ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ ሲሆን፣ እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ ሙሉ አቅም እንዳለው ተገልጿል።
​በምረቃው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  እንደተናገሩት፣ አውሮፕላን ማረፊያው የአካባቢውንና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እንዲሁም ቱሪዝምን ለማሳደግ አልሞ በሳምንት ሦስት በረራዎችን ያስተናግዳል።
​”የምንገነባው እያንዳንዱ አውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚ ያነቃቃል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በፈረንጆቹ 2026 80ኛ ዓመቱን የያዘውና የአፍሪካ ኩራት የሆነው አየር መንገድ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው ብለዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2