በፈንታሌ ወረዳ ከሦስት ወራት በላይ ባስቆጠረው የድርቅ አደጋ የከረዩ ማህበረሰብ ለከባድ ችግር መዳረጉ ተገለጸበኦሮሚያ ክልል ም…

- Advertisement -
Sidebar AD
❗️በፈንታሌ ወረዳ ከሦስት ወራት በላይ ባስቆጠረው የድርቅ አደጋ የከረዩ ማህበረሰብ ለከባድ ችግር መዳረጉ ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ስር በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ በርካታ የከረዩ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከቀዬአቸው መፈናቀላቸውንና ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።
አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ ድርቁ በሀሮ ቃርሳ፣ ዴቢቲ፣ ኢላላ፣ ቀረሪ፣ ጡጡጢ፣ ደጋ ሄዱ፣ ቆቦ፣ ባንቲ በተባሉ ቀበሌዎች ከሶስት ወር በፊት መከሰቱንና ነዋሪዎች ለብቶቻቸው ሳርና ውሃ ፍለጋ ከቀዬአቸው ተሰደዋል።
የወረዳው ነዋሪ የሆኑት አቶ ቁምቢ ኢዳኦ፤ በውሃና ጭድ እጥረት ምክንያት በርካታ ከብቶች እየሞቱ መሆኑን በመጥቀስ ከመንግስት በኩል “ምንም አይነት ርዳታ አለመኖሩ ችግሩን አባብሶታል” ብለዋል።
አክለውም አርብቶ አደሮቹ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለከብቶቻችን ምግብ ፍለጋ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ አለመቻላቸውንም ተናግረዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2