ኢትዮጵያዊያኑ ጠፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከጅቡቲ የተነሱ አራት ጀልባዎች ተገልብጠው 181 ኢትዮጵያዊያን መጥፋታቸው ተሰማ፡፡ የአለም የስደተኞች ድርጅት(አይኦኤም) እንደገለፀው ጀልባዎቹ ከጅቡቲ ተነስተው ወደየመን እየተጓዙ ነበር፡፡ አራቱም ጀልባዎች ጉዞ የጀመሩት ትላንት ሀሙስ ምሽት ላይ ሲሆን በወቅቱ የነሳው ሀይለኛ ንፋስ ጀልባዎቹን እንደገለበጣቸው አስረድቷል፡

፡ ከአራቱ ጀልባዎች ሁለቱ የተገለበጡት ጅቡቲ አቅራቢያ መሆኑን የገለፀው አይኦኤም በዚህኛው አደጋ ሁለት ስደተኞች ሞተው አስከሬናቸው መገኘቱን አስታውቋል፡፡

ቀሪዎቹ በጀልባው ላይ ተሳፍረው የነበሩት ስደተኞች በሙሉ በህይወት መትረፍ መቻላቸውንም ገልጿል፡፡ ሶስተኛው ጀልባ ከጅቡቲ ተነስቶ ጉዞ ከጀመረ በኋላ በደቡባዊ ምእራብ የመን ታኢዝ ግዛት ክልል ውስጥ ሲደርስ መገልበጡን ያስታወቀው ድርጅቱ በዚህኛው ጀልባ 31 ኢትዮጵያዊያንና ሁለት የመናዊያን የጀልባው አሽከርካሪዎች እንደነበሩ አስረድቷል፡፡

አራተኛው ጀልባም የተገለበጠው በዚሁ አካባቢ ሲሆን 150 ኢትዮጵያዊያንንና አራት የመናዊያን የጀልባውን አሽከርካሪዎች አሳፍሮ እንደነበር ጨምሮ ገልጿል፡፡

በመሆኑም በሶስተኛውና አራተኛው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩት 181 ኢትዮጵያዊያንና አምስት የመናዊያን የጀልባው አሽከርካሪዎች እስካሁን እንዳልተገኙ ጠቅሷል፡፡ እነዚህን የጠፉትን ሰዎች ፍለጋው እየተከናወነ ሲሆን አንደኛው የመናዊ መገኘቱንም አስረድቷል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አገራት ዜጎች ወደመካከለኛው ምስራቅ ለሚያደርጉት ፍልሰት ዋነኛ መተላለፊያቸው የመን ስትሆን በጅቡቲ በኩል በሚደረገው በዚህ ጉዞ በየአመቱ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች ሙከራ እንደሚያደርጉ ይገመታል፡፡

የመን ከመድረሳቸው በፊት በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የተለያዩ በደሎችና ብዝበዛዎች የሚደርሱባቸው ከመሆኑም በላይ ጉዟቸውም እጅግ አደገኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቀይ ባህርን ወይንም የኤደን ባህረ ሰላጤን የሚያቋርጡት በአነስተኛ ጀልባ ሲሆን በእነዚህ ጀልባዎችም በርካታ ሰዎችን አጨናንቀው ስለሚጭኑ እንደዚህ አይነት አደጋዎች የመከሰት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡

ባለፈው አስር አመት ውስጥ በዚህ መስመር እየተጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 2082 ያህሉ የጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ መስጠማቸው ከረጅም ጊዜ በኋላ የተረጋገጠው 693ቱ ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ አሁንም እንደጠፉ ናቸው፡፡
#zehabesha
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1