ሚኒስትሩ ምሽቱን ባወጣው በዚህ የጉዞ ማስጠንቀቂያ በህወሀት መካከል የተፈጠረውን ሽኩቻ ጠቅሶ በተለይ ወደአዲግራትና ዋና ከተማዋ መቀሌ ፈረንሳዊያን ፈፅሞ እንዳይሄዱ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሽኩቻ ወደጦር መሳሪያ ግጭት መለወጡን ጠቅሶም በዚያው የሚገኙ ፈረንሳዊያን በተቻለ ፍጥነት ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት የመጨመር ምልክቶች እየታዩበት መሆኑን የጠቀሰው ሚኒስትሩ በዚህ የተነሳ በአፋር ክልል ሰሜናዊ ክፍል አጋማሽ ድረስ ፈረንሳዊያን መሄድ እንደሌለባቸው አሳስቧል፡፡ በአፋር ክልል የሚገኘውን የአርታሌ እሳተ ጎመራ ለመጎብኘት እቅድ ያላቸው ፈረንሳዊያንም ፕሮግራማቸውን እንዲያራዝሙት ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
Source: Yeneta Tube









No comments yet.