#Ethiopia | ፈረሱ ኤንዶ ይባላል። 22 ዓመቱ ሲሆን፤ በግላኮማ እና በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ዓይኑን እንዳጣ ተንከባካቢው ሞርጋን ትናገራለች።
እጅግ ትወደው ስለነበር ውጤታማ እንዲሆን እንዴት መዝለል እና መጋለብ እንዳለበት ታሰለጥነው ነበር።
ኤንዶ ከሌሎች ፈረሶች ጋር ባደረገው የዝላይ ውድድር ሶስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን ችሏል።
ሁለቱንም ዓይኖቹን ቢያጣም፤ ኤንዶ ሶስት የጊነስ የዓለም ሪከርዶች ሻምፒዮን ሆኗል።
ከ13 ዓመቱ ጀምሮ ከጎኑ ከነበረችው አሰልጣኙ ሞርጋን ዋግነር ጋር በመሆን እነዚህን ጀብዱዎች አሳክቷል።
ሁለቱም ዓይኖቹ ማየት ሳይችሉ ስኬታማ መሆኑ ብዙዎችን ያስደነቀ እና ግራ ያጋባም ነበር።
ተንከባካቢው ሞርጋን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን አዳዲስ ነገሮችን እንዲላመድ እና እንዲሰለጥን ማድረጓ በራስ መተማመን እንዲያገኝ፣ የበለጠ ብቃቱን እንዲያሳይ እንደረዳው ትናገራለች።
የኤንዶ ታሪክ ብዙዎች መከራን ለማሸነፍ እንደ አበረታች ምሳሌ አድርገው እንደወሰዱት ይናገራሉ። ፈረሱ ዓይኑን ካጣ በኋላም ጥሩ ብቃትን ማሳየቱ ጽናቱን እና የሞርጋንን ውጤታማ የስልጠና ዘዴ አመላክቷል።
ተንከባካቢው ሞርጋን ማየት የማይችሉ ፈረሶች እንክብካቤ እንደሚሹ እና ይህን ካገኙም ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አፅንዖት ሰጥታ ተናግራለች። ሰዎች አቅማቸውን ከመገደብ ይልቅ በችሎታቸው ላይ እንዲያተኩሩ አሳስባለች።
ታዲያ ኤንዶ ዐይነ ሥውር እንስሳ ሆኖ አዕምሮው በዚህ ፍጥነት ካደገ፤ የሰው ልጅ አዕምሮን ከተጠቀመ ምን ይሳነዋል። ሁሉም ነገር በትምህርትና በስልጠና ከታገዘ ይቻላል የሚለውን ማሳያ ነው።
በሄለን ተስፋዬ
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et



Source: GetuTemesgen









No comments yet.