#Ethiopia | የድምጻዊት ሐይማኖት ግርማ አራተኛ አልበም ለአድማጭ ሊቀርብ ነው።
ከዚህ በፊት ሶስት አልበሞች ለአድማጭ ያቀረበችው ኦማሔሬ በተሰኘው የሙዚቃ ስራ ከአድማጮቿ ጋር የተዋወቀችው ሐይማኖት ግርማ አራተኛ አልበሟ ለህዝብ ልታደርስ ቀን ቆረሰጣለች።
አዲሱ አራተኛ አልበሟ 12 ያህል ትራኮች እንደያዘ የተናገረችው ድምጻዊቷ በርካታ የሙዚቃ ሰዎች እንደተሳተፉበት ተናግራለች።
ድምጻዊቷ ሙዚቃ በግል ጉዳይ ምክንያት ላለፉት 12 አመታት አቁማ የነበረ ቢሆንም በጓደኞቿ ምክንያት ዳግም ወደ ሙዚቃው አለም በመምጣት አራተኛ አልበሟ ለመስራት በቅታለች።
ታምሩ አማረ ሚኪ ጃኖና ሌሎችም ስመጥር የሙዚቃው ሰዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።
አልበሙን ሰርቶ ለመጨረስ አንድ አመት ቢቻ እንደወሰደባት የተናገረችው ሐይማኖት ግርማ በወጪም በኩል የተጋነነ ዋጋ አልተጠየኩበትም ብላለች።
አዲሱ አልበም ከበፊቶቹ አልበም እኩል እንዲደመጥ ጥራቱን ጠብቁ ተሰርቷል ነው የተባለው።
ሙዚቃውን ፕሮዲውስ ያደረገው ድምጻዊ ደሜ ሉላ አዲሱ የሐይማኖት ግርማ አልበም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጭ ይቀርባል ብሏል።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.