#Ethiopia | ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጅማ የደረሰው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ችቦ ደማቅ አቀባባል ተደረገለት።
ለዘጠኝ ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዘንድሮ በጅማ ከተማ አስተናጋጅነት ይደረጋል።
ከሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ መነሻውን ያደረገው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ችቦ በርካታ ከተሞችን አቋርጦ ዛሬ ጅማ ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የባሕል እና የስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ መኪዩ መሀመድን ጨምሮ በርካታ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ችቦው የተነሳበት የሲዳማ ክልል ለአዘጋጁ የጅማ ከተማ ችቦውን በደማቅ ስነ ስርዓት አስረክቧል።



Source: GetuTemesgen








No comments yet.