በሕገወጥ መንገድ የነዳጅ ቤንዝል በመኖርያ ቤቱ ያከማቸው ግለሠብ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት በሕገወጥ መንገድ የቤንዝል ነዳጅ በመኖሪያ ቤቱ ያከማቸ ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጥቷል።

የጅማ ከተማ ፖሊስ ኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት እንደገለፀው ተከሣሽ ነቢብ መሐመድ የተባለው ግለሠብ በጅማ ከተማ ወረዳ ሁለት ጊንጆ ቀበሌ ውስጥ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም በመኖርያ ቤቱ 7 መቶ ስድስት ሊትር ቤንዝል ሸሽጎ በማከማቸት በባለ ሁለት ሊትር ውሀ ፕላስቲክ እየቀነሰ ሲሸጥ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተከሳሹ በሕገወጥ መንገድ በመኖርያ ቤቱ ያከማቸውን ቤንዝል በድብቅ በከፍተኛ ዋጋ ሲሸጥ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው በፖሊስ ሲጣራ ቆይቶ ለአቃቢ መዝገቡ ተልኳል።

አቃቢ ሕግ የነዳጅ ምርቶችና ውጤቶችን ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር የወጣውን መመርያ ደብ ቁጥር 1363 /2017 ንኡስ አንቀፅ 2 በመጥቀስ ክስ መስርቷል።

በአቃቤ ሕግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የጅማ ከተማ ወረዳ ሁለት ፍርድ ቤት ተከሳሹን በሁለት ዓመት እስራት እና በሀያ ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: