ሩሲያ አሜሪካ እያሳደደቻት ላለችው የነዳጅ መርከብ የባህር ኃይል ጥበቃ መድባለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ሩሲያ፤ በአሜሪካ ኃይሎች እየተሳደደች ለምትገኘው እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የምትጓዝ የነዳጅ መርከብን ለማጀብ የባህር ኃይሏን ማሰማራቷን ቢቢሲ (BBC) እና ሲቢኤስ (CBS) ዘግበዋል።

​የጉዳዩ ዝርዝር፡-

​🚢 የመርከቧ ማንነት፡

ቀደም ሲል “ቤላ 1” (Bella 1) ትባል የነበረችው ይህች መርከብ፤ አሁን ስሟን ወደ “ማሪኔራ” (Marinera) የቀየረች ሲሆን፤ ባንዲራዋንም ከጉያና ወደ ሩሲያ ቀይራለች። መርከቧ በአሁኑ ሰዓት ባዶዋን ብትሆንም በተለምዶ የቬንዙዌላን ድፍድፍ ነዳጅ በማጓጓዝ ትታወቃለች።

​📍 አሁን ያለችበት ሁኔታ፡

መርከቧ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስኮትላንድ እና በአይስላንድ መካከል እንደምትገኝ ተጠቁሟል።

​🇺🇸 የአሜሪካ አቋም፡

​አሜሪካ መርከቧን “የማዕቀብ ጥሰት የፈፀመች” በማለት ለመውረስ እየተከታተለች ነው።

​ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ አሜሪካ መርከቧን ከመስጠም ይልቅ ለመውረስ (To seize) እቅድ አላት።
​የአሜሪካ ደቡባዊ ዕዝ (Southern Command) እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

​🇷🇺 የሩሲያ ምላሽ፡
​ሩሲያ ሁኔታውን “በስጋት እየተከታተለች” መሆኑን ገልጻለች።
​”መርከቧ የሩሲያን ባንዲራ እያውለበለበች ዓለም አቀፍ ህግን አክብራ እየተጓዘች ነው፤ አሜሪካ እና ኔቶ ትኩረት ሊነፍጓት አይገባም” በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

​የማዱሮ ጉዳይ እና የትራምፕ ትዕዛዝ፡

ይህ ክስተት የተፈጠረው አሜሪካ የቬንዙዌላውን የቀድሞ መሪ ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ስር ካዋለች እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማዕቀብ የተጣለባቸውን የነዳጅ መርከቦች “እንዲታገዱ” (Blockade) ካዘዙ በኋላ ነው።

​ሁኔታው በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል በቀጥታ ግጭት ሊያስከትል የሚችል ስጋት ፈጥሯል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

​#Russia #USA #OilTanker #Tension #Venezuela #BreakingNews #Marinera


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: