🙏
* ”የህዝቡ ቅሬታ ተገቢ ነው፤ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ!”
#Ethiopia | በትላንትናው እለት በወንድሜ በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን በገለጽኩበት ቪዲዮ ላይ፤ ከወዳጄ ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ጋር ያደረግኩትን የግል የስልክ ልውውጥ አካትቼ ማቅረቤ ይታወሳል።
ይሁንና ይህን የድምፅ መልዕክት ማካተቴ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን፣ የሟች ቤተሰቦችን እና የሙያ አጋሮቼን ቅር እንዳሰኘ ተረድቻለሁ። ቅሬታውም ተገቢ እና ትክክል ነው ብዬ ስላመንኩ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን እና አድናቂዎቼን በትህትና ይቅርታ እጠይቃለሁ።
በድጋሚ በወንድሜ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ እልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ፤ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ መፅናናትን እመኛለሁ።
ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን! 🕯️
ገነት ንጋቱ
#Apology #GenetNigatu #NetsanetWorkneh #Ethiopia #Respect
Source: GetuTemesgen









No comments yet.