#ExitExamበ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች የፈተና ጊዜ ተራዝሟል፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ለከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
#ExitExam
በ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች የፈተና ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ የዚህ ዓመት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ከጥር 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል።
ነገር ግን “ከፈተና ዝግጅት ሥራዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት” የፈተናው ቀን የተራዘመ መሆኑ ተገልጿል።
ምዝገባ ያደረጋችሁና በማድረግ ላይ የምትገኘ ተመዛኞች ፈተናው የሚሰጥበት ትክክለኛ ቀን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት / በትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ በትዕግስት አንድትጠብቁ ተብሏል።
(ከላይ የተያያዘው የምስል መረጃ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።)
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1