ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ ጭማሪ ማወቅ ያለብዎ ሕጋዊ ነጥቦች!
በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ (ቁጥር 1320/2016) መሠረት፣ የአከራይና ተከራይ መብትና ግዴታዎች በግልጽ ተቀምጠዋል። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች እነሆ፦
1. የኪራይ ዋጋ ጭማሪን በተመለከተ
የጊዜ ገደብ፦ አከራይ የኪራይ ዋጋ መጨመር የሚችለው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
የጭማሪ መጠን፦ ጭማሪው የሚወሰነው በከተማ አስተዳደሩ በሚወጣ የዋጋ ማውጫ (Index) መሠረት እንጂ አከራይ በፈለገው መጠን አይደለም።
ማስጠንቀቂያ፦ ዋጋ ለመጨመር ውሉ ከማለቁ 2 ወራት በፊት ለተከራዩ በጽሁፍ ማሳወቅ ግዴታ ነው።
2. የኪራይ ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች
የኪራይ ውል በጊዜው ሲያልቅ የሚበቃ ቢሆንም፣ በውሉ መሃል ግንኙነቱን ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት መንገዶች ብቻ ነው፦
ሀ. በስምምነትና በማስጠንቀቂያ፦
በስምምነት፦ ሁለቱም ወገኖች ተስማምተው በማንኛውም ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ።
ቤት ሲተላለፍ፦ የቤቱ ባለቤትነት በሽያጭ ወይም በውርስ ለሌላ ሰው ከተላለፈ፣ አዲሱ ባለቤት የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ማስለቀቅ ይችላል።
ተከራይ ሲፈልግ፦ ተከራዩ በማንኛውም ጊዜ ለባለቤቱ የ2 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል።
ለ. ያለ ማስጠንቀቂያ (በጥፋት ምክንያት)፦
ተከራይ የሚከተሉትን ከፈጸመ ውሉ ወዲያውኑ ይቋረጣል፦
የኪራይ መክፈያ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ 15 ቀናት፣ ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ 7 ቀናት ካለፈ።
ቤቱን ከአከራይ ፈቃድ ውጪ ለንግድ ወይም ለሌላ አገልግሎት ካዋለ።
የአካባቢውን ሰላም በተደጋጋሚ ካወከና በቤቱ ውስጥ ወንጀል ከፈጸመ።
በቤቱ ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ።
3. ክርክሮችን ማን ይወሰናል?
ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ የሚነሱ ክርክሮችን ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን የላቸውም። ይልቁንም ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የተሰጠው ለቤቶች አስተዳደር ተቆጣጣሪ አካል (ለምሳሌ፦ በአዲስ አበባ የወረዳ ወይም የክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት) ነው።
ማሳሰቢያ
ይህ አዋጅ ተፈጻሚ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት ብቻ ነው። ለንግድ ቤቶች ወይም ለሌላ አገልግሎት የተከራዩ ቤቶችን አይመለከትም።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.