የ“ሻዶ ባትሪ” የፈጠራ ቪዲዮ ውድድር በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

ባለፉት 45 ቀናት በቲክቶክ መንደር ከፍተኛ መነቃቃትን ሲፈጥር የነበረው የ“ሻዶ ባትሪ” የፈጠራ ቪዲዮ ውድድር ባሳለፍነው ሚያዝያ 5/2018 ዓ/ም ምሽት በአዲስ አበባ ማርዮት ሆቴል በተካሄደ ደማቅ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል።

በዙሚ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ (Zumi Industry PLC) የተዘጋጀው ይህ ልዩ ዘመቻ፣ ከ3,000 በላይ የፈጠራ ሥራዎች የቀረቡበት ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች አቅም ያሳየ መድረክ ሆኖ አልፏል።

​በዕለቱ በተካሄደው የሽልማት መርሃ-ግብር ​ለአሸናፊዎች በአጠቃላይ 3,200,000 (ሦስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ) ብር የገንዘብ ሽልማት ለአሸናፊዎቹ ተበርክቷል።

​በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ የቲክቶክ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የዕውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።

​ይህ ውድድር በዓይነቱ ለየት ያለና ከፍተኛ ተሳትፎ የታየበት ሲሆን፣ የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

በመጨረሻም ዝግጅቱ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ አዘጋጆቹ ለተሳታፊዎችና ለደጋፊዎቻቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአዘጋጁ የውድድር መሥፈርት መሠረት በቲክቶክ ስሟ ቦቲና በመባል የምትጠራዋ ሳባ ወንድማገኝ ሙሉጌታ 3.6 ሚሊየን ተመልካች በማግኘት 1ኛ ሆና አሸንፋ 400 ሺ ብር ሽልማት ተቀብላለች

ሁለተኛ ቲክቶከር ታምራት ጌታቸው ሲሆን 3.3 ሚሊየን ተመልካች በማግኘት የ300 ሺ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

ሶስተኛ የወጣችው አዪልነሽ ፋንታው ስትሆን የ200 ሺ ብር ተሸላሚ ሆናለች።

አያልነሽ ባደረገችው አሳዛኝ ንግግር ዩ ሀቭ ሶፕ ዲተርጀንት ኤንድ ሞርያ ድርጅት እያንዳንዳቸው መቶ መቶ ሺ ብር እና ከቲክቶከር ጃኒ የ50 ሺ ብር ተጨማሪ ስጦታ ተበርክቶላታል።

የሻዶ ባትሪ ቻሌንጅ ላይ ጥሩ ውጤት ያመጡ 12 ተወዳዳሪዎችም ከሻዶ ባትሪ እያንዳንዳቸው የመቶ መቶ ሺ ብር ሽልማታቸውን ወስደዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: