የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር

- Advertisement -
Sidebar AD

ያለበት አልታወቀም ተባለ

#Ethiopia | ከአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ መታገት ጀርባ ያለው ምስጢር ምንድን ነው? ቤተሰቦቹ በከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው።

መግለጫ

የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው ሚሊዮን በየነ በቁጥጥር ስር ከዋለ/ከተወሰደ 24 ሰዓታት ሊሞላው ቢቃረብም፣ እስካሁን የት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም። ይህ ሁኔታ በቤተሰቦቹ ዘንድ ከፍተኛ ጭንቀትና ስጋት ፈጥሯል።

የጋዜጣው አሳታሚ ጃከን ፐብሊሺንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባወጣው መግለጫ የሚከተሉትን ነጥቦች አሳስቧል፦

ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሚሊዮን ያለበትን ቦታ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁ።

ደህንነት፦ የሚሊዮን ደህንነት ተጠብቆ በአፋጣኝ ወደ ቤተሰቦቹ እንዲመለስ አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ እንዲወሰድ ድርጅቱ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።

“የሚሊዮን ደህንነት የሁላችንም ስጋት ነው፤ ያለበት ቦታ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን!” — ጃከን ፐብሊሺንግ

#Update Statement on Our Missing Colleague

Nearly 24 hours after he was taken, the whereabouts of Million Beyene, Managing Editor of Addis Standard, remain unknown.

His family is increasingly distressed and deeply concerned for his safety.

JAKENN Publishing PLC renews its urgent call on the relevant authorities, including the Addis Ababa Police, the Federal Police Commission, and the Ethiopian Human Rights Commission, to act without delay to establish his whereabouts and ensure his safe and immediate return.


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: