የባሕር በር አልባነት በኢትዮጵያ ብልጽግና ላይ ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ ይቀጥላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባሕር በር አልባነት እና ሎጂስቲክስ ውስንነት በኢትዮጵያ ብልጽግና ላይ ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ ይቀጥላል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል መሪ ሐሳብ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ በባሕር በር ጉዳይ ላይ ግራ ቀኝ የሚሉ ዜጎችን ስመለከት ይገርመኛል ብለዋል።

የባሕር በር ጉዳይ የመንግስት ሳይሆን በእያንዳንዱ ዜጋ ህይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው÷ በፍትሃዊ ዋጋ ልንገበያይ የምንችለው ምግብ፣ አልባሳት እና መድሃኒት ወደብ በማጣታችን ምክንያት ዋጋቸው ሲጨምር ይታያል ነው ያሉት።

በዓለም 10ኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ታላቅና ወደብ አልባነት ችግር ያልነበራት ሀገርን በክፋትና በሰጥቶ መቀበል መርህ ባለማመን ወደብ አልባ አድርጎ መቀጠል በየትኛውም ዘመን አዋጭ አይደለም ብለዋል።

ችግሩን በመነጋገርና ሁሉን አሸናፊ በሚያደርግ መንገድ መፍታት ካልተቻለ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራትም ጭምር አዋጭ እንደልሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት፡፡

በመሆኑም በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትም ሆኑ የዓለም ሀገራት በትኩረት ማሰብ አለባቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ከአጭር ጊዜ አንጻር የደረቅ ወደብ በድሬዳዋ እና ሞጆ እንዲሁም የንግድ ቀጣናዎችን በጂቡቲ በማስፋት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ቁሶችን ለማቀላጠፍ እና ዋጋቸውን ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከረጅም ጊዜ አንጻር ግን በየትኛውም መንገድ ኢትዮጵያን የወደብ ባለቤት ማድረግ ካልተቻለ ብልጽግናን ማረጋገጥም ሆነ የቀጣናውን ሰላም ጠብቆ ማስቀጠል እንደይማቻል አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

FBC


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: