195 ህፃናት አዲስ ሕይወት ሊያገኙ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

* የ “ኸርት ቱ ኸርት” እና የጤና ሚኒስቴር ታሪካዊ ስምምነት

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ስምምነት ተፈርሟል። “ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ” (Heart to Heart Children’s Aid) ለ195 ህፃናት ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴር እና ከስምንት ታላላቅ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

​የህክምናው ተጠቃሚዎች
በአጠቃላይ 195 ህፃናት (175 በአዲስ አበባ እና 20 በጅግጅጋ) ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ያገኛሉ።

​የሆስፒታሎች ርብርብ፦

​ጥቁር አንበሳ (50)፣
የልብ ህሙማን መርጃ (50)፣
ኢትዮ ኢስታንቡል (70)፣
ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ (25)፣
እንዲሁም ኤልውዘር (5) ህፃናትን ተቀብለው ያክማሉ።

​የዘመቻው ጊዜ፦
ህክምናው ከሚያዝያ 12 ጀምሮ ለ45 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የጅግጅጋው ጉዞ ነገ ሚያዝያ 9/2018 ዓ.ም ይጀመራል።

​ዓለም አቀፍ ትብብር፦
ከጣልያን የሚመጡ ባለሙያዎች ሚያዝያ 16 ቀን የኢትዮጵያዊያኑን የህክምና ቡድን ይቀላቀላሉ።

​ ታካሚዎች እንዴት ይመረጣሉ?

ምርጫው ያለምንም አድልኦ፣ በኢትዮጵያ የልብ ማህበር በኩል ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ባሉ ህጻናት ቅደም ተከተል መሰረት በጥንቃቄ ይከናወናል።

​በኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና! 🙏

​#getu #HeartToHeart #EthiopiaHealth #ChildHeartSurgery #MedicalCampaign #AddisAbaba #Jijiga #MinistryOfHealthEthiopia #SavingLives #HopeForChildren #በጎአድራጎት #የልብህክምና #የህፃናትጤና #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1