#Ethiopia | የዓለም ባንክ ይፋ ባደረገው አዲስ አህጉራዊ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና የሚያሳይ አሳሳቢ አኃዝ ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ እንደሚጠቁመው፣ ኢትዮጵያውያን ከአጠቃላይ ወጪያቸው ውስጥ ከ58.5 በመቶ በላይ የሚሆነውን ለምግብ ፍጆታ ብቻ ለማዋል ተገደዋል።
የዋጋ ንረቱ የከተማ ነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ በገጠር የሚገኙ ዜጎችንም በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ ይገኛል። የሸቀጦች ዋጋ መጨመር በገጠር ያለውን የኑሮ ሚዛን እያናጋው መሆኑ ተመልክቷል።
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ቀውስ የነዳጅ ዋጋን በመጨመር፣ በሀገር ውስጥ ያለውን የትራንስፖርትና የምርት ዋጋ ይበልጥ ሊያናረው እንደሚችል ባንኩ አስጠንቅቋል።
ይህ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከምግብ ዋስትና ጋር ተዳምሮ የዜጎችን የመግዛት አቅም ይበልጥ ሊያዳክም እንደሚችል ተጠቁሟል።
ይህ መረጃ እንደሚያሳየው፣ የኑሮ ውድነቱ ከምግብ ፍጆታ አልፎ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ የራሱን ጫና ማሳረፉን ቀጥሏል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ebs #Ethiopia #Economy #WorldBank #Inflation #FoodSecurity #NewsUpdate #LeadThePlot #AddisAbaba #GlobalEconomy
Source: GetuTemesgen








No comments yet.