በፊንቴክ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ!ሚያዝያ 9፣ 2018 በፊንቴክ የኢንቨስትመንት ስም በተፈጸ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በፊንቴክ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ!
ሚያዝያ 9፣ 2018 በፊንቴክ የኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ መጠነ ሰፊ የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዛሬ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
መርማሪ ፖሊስ ላለፉት ቀናት ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ሂደት ለችሎቱ ያስረዳ ሲሆን፣ በቀጣይም የሚከተሉትን ነጥቦች ለማከናወን ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፦
* የወንጀሉን ውስብስብነት እና ስፋት መመርመር፤
* የተጭበረበረውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ማረጋገጥ፤
* ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ደንበኞቻቸው በዋስ እንዲፈቱ ጠንካራ መከራከሪያዎችን አቅርበዋል።
ከነዚህም መካከል፦
1. ተጠርጣሪዎቹ ታዋቂ እና ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ የመሰወር ስጋት የሌለባቸው መሆኑ፤
2. መደበኛ ስራ እና መተዳደሪያ ያላቸው መሆኑ፤
3. አንዳንድ ተጠርጣሪዎች ያሉባቸውን የጤና እክሎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል።
ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ በፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
እስከዚያው ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራቸው እንደሚቀጥል ታውቋል።ጉርሻ page
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1