ቴዲ አፍሮ በ”ኢቶሪካ” የሙዚቃ አልበም የኢትዮጵያን የሙዚቃ ሰንጠረዥ አነቃነቀው፤ በአንድ ቀን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እይታዎች ተመዝግበዋል
#FastMereja I ቴዲ አፍሮ አዲስ ባወጣው “ኢቶሪካ” የተሰኘ አልበም የሀገሪቱን የሙዚቃ ሰንጠረዥ በከፍተኛ ደረጃ ተቆጣጥሯል። በየኔ ቫይብ (YeneVibe.com) ሳምንታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ እንደታየው፣ ድምፃዊው ከአስሩ ቀዳሚ ስራዎች ውስጥ ዘጠኙን ደረጃዎች በብቸኝነት በመያዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
አልበሙ በወጣ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩቲዩብ እይታዎችን ያገኘ ሲሆን፣ በተለይም “ዳስ ጣል (አንሳው)” የተሰኘው ስራው ከ5.3 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን በማግኘት የሳምንቱ ቀዳሚ ሆኗል።
በዚህ ሳምንት በየኔ ቫይብ ከፍተኛ እይታ የተመዘገበላቸው ቀዳሚ 10 ሙዚቃዎች ዝርዝር፦
1ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ዳስ ጣል (አንሳው): 5,333,181 እይታዎች
2ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ጀምበር: 3,279,195 እይታዎች
3ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – መሬማ: 2,444,573 እይታዎች
4ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ጽዮን ሙሽራዬ: 2,201,619 እይታዎች
5ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ስምምነን (ጉራጌ): 2,108,460 እይታዎች
6ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ስማ እራሴ: 1,785,734 እይታዎች
7ኛ ✅ ዮ ማሪዮስ – ድግስ ነው: 1,780,624 እይታዎች
8ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ኢቶሪካ: 1,713,367 እይታዎች
9ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – ሺ ቢባል (ወደ 90ዎቹ): 1,664,424 እይታዎች
10ኛ ✅ ቴዲ አፍሮ – መርከብ: 1,662,264 እይታዎች
የየኔ ቫይብ የደረጃ ሰንጠረዥ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ የዲጂታል ሲስተም ከዩቲዩብ እይታዎች ተሰልቶ የሚቀርብ ነው። ሙሉውን 100 የሙዚቃ ዝርዝር ለመመልከት የYeneVibe ድረ-ገጽን መጎብኘት ይቻላል።
Source: FastMereja









No comments yet.