ድንቅ ድንቅ ተአምራትን የሚያደርጉ የፈውስ አባት

- Advertisement -
Sidebar AD

ድንቅ ድንቅ ተአምራትን የሚያደርጉ የፈውስ አባት🙏

ከካህኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1212 ዓ.ም እቲሳ ደብረ ጽላልሽ ተወለዱ፡፡

የስማቸው ትርጓሜ የሃይማኖት ተክል፣ የጽድቅ ፍሬ ያፈራ፣ ምእመናንን በቃለ ወንጌል ያጣፈጠ ቅመም፣ መዓዛ ሕይወቱ የሚማርክ፣ የጻድቃን መጠለያ ተክል የሚል ነው፡፡ አንድም ተክለ ሃይማኖት ማለት “የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል” ማለት ነው፡፡ ወላጆቻቸው ፍሥሐ ጽዮን ቢሏቸውም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ተክለ ሃይማኖት ብሏቸዋል፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌል በመስበክና ተአምራት በማድረግ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ መንገድ መልሰዋል፤ አቢያተ ክርስቲያናትም አንጸዋል፡፡ ሕገ ወንጌልን እየተዘዋወሩ የሚያስተምሩ ሰባኬ ወንጌል፤ በክርስቶስ ስም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን የሚደርጉ የፈውስ አባት በመሆናቸውም ሐዲስ ሐዋርያ ተብለዋል። ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው፣ በብሕትውና ኖረዋል፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በወጣትነት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ በበርካታ የሀገራችን ክፍሎች በተለይ በደቡቡ አካባቢ ተዘዋውረው ወንጌል ሰብከዋል።

ሕዝቡንና መሳፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው ጠንቁዋዮችንና የጣኦት አምልኮትን አጥፍተዋል፡፡ አባታችን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የሞላባቸው ቢሆኑም በገዳማዊ ሕይወታቸው ግን በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳማትና፣ በደብረ ዳሞ ከአባ ዮሐኒ ጋር፣ በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከደብረ ዳሞ ተሰናብተው ሲወጡም የሚወርዱበት ገመድ ቢበጠስ እንደ ሱራፊ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ቅዱሳን መካናትን አይተዋል፤ ሙት አንስተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ በርካታ ደቀ መዛሙርት አፍርተው ደብረ ሊባኖሰን መስርተዋል፡፡ ዛሬም በርካታ የመንፈስ ልጆቻቸው በየገዳማቱ ወድቀው ይጸልያሉ፡፡ ገዳማትንና ገዳማውያንን መደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ ያደርገናል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: